How do we stay useful in changing times?
AFLEX President Mr. Zadig Abrha breaks down:
Reform, Scaling up and Transformation at the levels of individuals, organizations and nations
Institutional integrity as the foundation of success
https://www.youtube.com/watch?v=wHYVm6PCPkE
በአዲሱ ዓለም ራስን ጠቃሚ አድርጎ የማቆየት ጥበብ ምንድን ነው? – ከግለሰብ እስከ ሀገር
በአዲሱ ዓለም ራስን ጠቃሚ አድርጎ የማቆየት ጥበብ ምንድን ነው? – ከግለሰብ እስከ ሀገር
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለአመራሮች
በአዲሱዓለምራስንጠቃሚአድርጎየማቆየትጥበብምንድንነው?ከግለሰብ እስከ_ሀገር
በሚል ርዕስ በሰጡት ስልጠና ላይ የተካተቱ ሀሳቦች ምንድን ናቸው?
👉 ለውጥ (Reform)፤ ማስፋት (Scaling-up) እና ሽግግር (Transformation) ምንድን ናቸው? ለግለሰብ፤ ለቡድን፤ ለሃላፊ፤ለተቋማት፤ ለሀገር የሚኖራቸው ሚና ምንድን ነው?
👉 በአንድ ስርዓት ውስጥ ተንጋዶ የበቀለውን ነገር ማስተካከል ለውጥ (Reform) ነው።
👉 ተሰርቶ ውጤት የተገኘበትን ነገር ለሌሎች የማዳረስ ተግባር ማስፋት (Scaling-up) ይባላል።
👉 መሰረታዊ እና ጥልቅ ለውጥ በማድረግ የስርዓቱን መሰረታዊ ባህርይ መቀየር ሽግግር (Transformation) ነው።
👉 አብርሀም ሊንከንን የህይወት ዘመን የአሜሪካ ተወዳጅ ፕሬዚደንት ያደረገው ተግባር ምንድን ነው?
👉 የፎርድ መኪና አምራች ኩባንያ በመኪና ገዥዎች ልብ ውስጥ በታማኝነት ታትሞ እንዲቀር ያደረገው መቼ እና እንዴት የፈጸመው ተግባሩ ነው?
👉 ፓታጎኒያ ቃሉን ጠብቆ በመቆየቱ የትርፍ ህዳጉ በየዓመቱ 15% እያደገለት ዓመታትን ተሻግሯል። ምስጢሩ ምን ይሆን?
👉 ማዘር ተሬሳ ተወዳጅ ሆነው የዘለቁትና ስማቸውና ተግባራቸው ከትውልድ ትውልድ የተሻገረው ለምን ይሆን?
👉 ከባለታሪኮቹ ምን እንማራለን? ተንጋዶ የበቀለውን ለማስተካከል ምን አደረግን? ጥሩ ውጤት አምጥተን ያስጨበጨብንለትን ተግባር ወዴት አሻገርነው? ያስቸገረንን ሰንኮፍ ነቅለን የባህርይ ለውጥ ያመጣነውስ በየትኞቹ ስራዎቻችን ላይ ነው?
👉 የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ
በአዲሱዓለምራስንጠቃሚአድርጎየማቆየትጥበብምንድንነው?ከግለሰብ እስከ_ሀገር
በሚል ርዕስ በሰጡት ስልጠና ላይ ሰፊ ማብራሪያ አላቸው። ሙሉውን ከቪዲዮው ያገኙታል።